“ እራሴን መጉዳት ፈልጌ ነው “ፔፕ ጋርዲዮላ
አስከፊ የውድድር አመት በማሳለፍ ላይ የሚገኙት የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ፊታቸውን አውቀው በንዴት እንዳበላሹት ተናግረዋል፡፡
ከትናንት ምሽቱ የአቻ ጨዋታ በኋላ ስፔናዊው የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣን ፔፕ ጋርዲዮላ በንዴት ፊታቸውን አውቀው እንደቦጫጨሩት ተናግረዋል፡፡
የውጤት ማጣት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ በምሽቱ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ፌኖርድን አስተናግዶ 3ለ0 መምራት ቢችልም ውጤቱን ሳያስጠብቅ ቀርቶ አቻ መለያየቱ ይታወሳል፡፡
በቡድናቸው ውጤት የተበሳጩት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከጨዋታው በኋላ እንደተናገሩት ፊቴን በጣቶቼ ያበላሸሁት አውቄ ነው፤እራሴን መጉዳት እፈልጋለሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም አሰልጣኙ እንዳሉት ስለ ጨዋታው ክስተት ለተጨዋቾቼ ምንም ነገር ማናገር አልፈልግም፤ምክንያቱም ሁሉንም ነገር ጠንቅቀው ያውቁታል ብለዋል፡፡
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ታሪክ አንድ ክለብ 3ለ0 እየመራ ከ75ኛው ደቂቃ በኋላ ግብ ተቆጥሮበት የወጣ የመጀመሪያው ክለብ ማንችስተር ሲቲ ሆኗል፡፡
ተከታታይ ያለፉትን ስድስት ያህል ጨዋታዎችን ሶስት ነጥብ ማሳካት የተሳነው ማንችስተር ሲቲ በሻምፒዮንስ ሊጉ አሸንፎ ወደ መረጋጋት ይመለሳል ቢባልም ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡
እጅግ አሰቸጋሪ የውድድር አመት በማሳለፍ ላይ የሚገኙት ሲትዝኖቹ በሳምንቱ መጨረሻ ቀን እሁድ ከፕሪሚየር ሊጉ መሪ ሊቨርፑል ጋር በአንፊልድ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
✍️ይገደብ አባይ
@Bisrat_Sport_433et@Bisrat_Sport_433et