View in Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF : ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተሰጥቶታል። @tikvahethiopia
#TPLF " አልቀበልም ! " - ህወሓት ህወሓት የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ የሰጠውን የምዝገባ ውሳኔ አልቀበልም አለ። ድርጅቱ " የተሰጠኝ የምዝገባ ውሳኔ ከተካሄዱት የሁለትዮሽ ወይይቶችና መግባባት ወጪ ነው፤ ስለሆነም ወደ ነባሩ እውቅናዬ የማይመልስ ውሳኔ አልቀበልም " ብሏል ዛሬ ነሀሴ 4/2016 ዓ.ም ባወጣው ባለ ሁለት ገፅ የፅሑፍ መግለጫ። ህወሓት ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዞ ቀርቧል። ትላንትና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፓርቲዎች " በልዩ " ሁኔታ ሲመዘገቡ የሚሰጥ ሕጋዊ የሰውነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መስጠቱ ይታወሳል። ይህን ውሳኔ ነው ህወሓት " አልቀበልም " ብሎ መግለጫ ያወጣው። " እኛ የምፈልገው የተሰረዘው ህጋዊ ሰውነታችን እንዲመለስልን ብቻ ነው " ብሏል።
@tikvahethiopia
Share
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Find friends or serious relationships easily
Start