🇷🇺🇳🇪 ሩሲያ እና ኒጀር በኢነርጂ እና በመሰረተ ልማት ላይ ትኩረት በማድረግ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ፤ ከኒጀር ጠቅላይ ሚኒስትር አሊ ማሃማኔ ላሚን ዜይን እና የኒጀር ሪፐብሊክ ርዕሰ መስተዳድርና የሀገር ውስጥ መከላከያ ብሔራዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር አብዱራህማን ቺያኒ ጋር በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ ተገናኝተው ተወያይተዋል።
ሀገራቱ አንዱ ሌላውን ወሳኝ አጋር አድርገው እንደሚቆጥሩ በውይይቱ ወቅት ተገልጿል።
በኢነርጂ፣ በግብርና፣ በመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች፣ በስነ-ምድር አሰሳ እና በማዕድን ክምችት ልማት ላይ ተግባራዊ ትብብርን መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል። በሰብዓዊ ዘርፍ ትምህርት፣ ባህልና ስፖርትን ጨምሮ ትብብርን በማጠናከር ዙርያም መክረዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኖቫክ፤ በቅርቡ በሴንት ፒተርስበርግ የተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ፤ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለውን ትብብር እንዳሳደገና የኢነርጂ እና የትራንስፖርት መሠረተ ልማትን ጨምሮ፤ የህይወት ጥራትን ማሻሻል ላይ ያተኮሩ የጋራ ፕሮጀክቶች እንዲጠናከር ማድረጉን ተናግረዋል።
ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- 👉 APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia