Смотреть в Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ትግራይን ዳግም ወደ ጦርነት የሚያስገባ ተጨባጭ ስጋት አለ ? " ይሄ የአንድ ድርጅት ጉዳይ ነው። ወደ ጦርነት የሚያስገባ ምንም ነገር የለም " - አቶ አማኑኤል አሰፋ በሊቀ - መንበሩ ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የ14ኛው የህወሓት ጉባኤ ቃል አቀባይ አማኑኤል አሰፋ ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ጦርነት የሚያስገባ ነገር የለም ብለዋል። አቶ አማኑኤል ፥ " በአንድ አዳራሽ ውስጥ ገብቶ…
#TPLF በሊቀመንበሩ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የተመራው የህወሓት ጉባኤ አቶ ጌታቸው ረዳን ከምክትል ሊቀመንበርነት አነሳ። ዶ/ር ደብረጽዮን በድጋሚ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ተነግሯል። በአቶ ጌታቸው ረዳ ምትክ አቶ አማኑኤል አሰፋ ምክትል ሊመንበር ሆነው ተመርጠዋል። ሌሎች የስራ አስፈጻሚና የማእከላይ ኮሚቴ ሆነው የተመረጡ የድርጅቱ አባላት ከላይ ስማቸው ተያይዟል። ምርጫ ቦርድ ከጉባኤው ቀደም ብሎ የቦርዱን አሰራር ያልተከተለ ጠቅላላ ጉባኤ እና በጉባኤው የሚተላለፉ ማንኛውም ውሳኔዎች ተቀባይነት እንደማይኖረው አሳውቆ ነበር። @tikvahethiopia
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Бот для знакомств