#የቀጠለ 🔴 ቁጥራዊ መረጃዎች
⚪️🎯 || የክለባችን ተጋጣሚ የሆኑት ክርስትያል ፓላሶች በባለፈው ውድድር አመት ግንቦት ወር ላይ ክለባችንን 4-0 ያሸነፉ ሲሆን ይህም ክለባችንን በሰፊ ውጤት ያሸነፉበት ጨዋታ ሆኖ ተመዝግቦላቸዋል ይህንን ከዚህ ቀደም ያረጉት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 1972 ላይ ነበር።
🎯 || ባለፈው ውድድር ክሪስትያል ፓላሶች ለመጀመርያ ጊዜ ክለባችንን ለሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ድል ማድረግ ችለዋል። በመጀመርያው 1-0 በቀጣዩ 4-0 ዛሬ ክለባችን ይህን መጥፎ ሪከርድ ለመግፈፍ ሴልኸርስት ፓርክ ያቀናል።
🎯 || ክለባችን ማንችስተር ዩናይትድ ወደ ሴልኸርስት ፓርክ አቅንቶ ባደረጋቸው ያለፉት አራት ያክል የሊጉ ጨዋታዎች ምንም አይነት ድል ያላስመዘገበ ሲሆን በሁለቱ ሲሸነፍ ፣ በሁለቱ ደግሞ አቻ ተለያይቷል።
🎯 || እንዲሁም ክለባችን ማን ዩናይትድ ከለንደም ክለቦች ጋር በሜዳው ባደረጋቸው ያለፉት 16 የሊጉ ጨዋታዎች ያሸነፈው ሁለቱን ያክል ብቻ ነው ፣ በአራቱ አቻ ሲለያይ በአስሩ ሽንፈትን አስተናግዷል።
🎯 || የክለባችን ማንችስተር ዩናይትድ ኔዘርላንዳዊ አሰልጣኝ የሆኑት ኤሪክ ቴን ሀግ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ከሜዳቸው ውጪ ባደረጉት ያለፉት 40 ያክል ጨዋታዎች 17 ሲያሸንፍ እንዲሁም 17 ተሸንፈዋል እንዲሁም በቀሪዎቹ ስድስት ጨዋታዎች በአቻ አጠናቀዋል።
በዛሬው እለትስ ምን እንመለከት ይሆን ? ምሽት 1:30 ሁሉን ነገር ይነግረናል።
#ይቀጥላል...
@man_united_ethio_fans@man_united_ethio_fans