አራዳ Exclusive !!
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የምስል መብት ባለቤት የሆነው ሱፐር ስፖርት የ3ኛ ሳምንት የሊጉን መርሐ-ግብሮች እንደማያስተላልፍ ታውቋል።
ዘንድሮን ጨምሮ ያለፉትን አራት ዓመታት የሀገራችንን ከፍተኛው የሊግ ዕርከን ውድድር የምስል መብት የገዛው ሱፐር ስፖርት በአንድ ከተማ የሚደረገውን የሊግ ውድድር ለአድማጭ ተመልካቾች ሲያደርስ እንደነበር አይዘነጋም።
ዘንድሮ የውሉ ማብቂያ ላይ የሚገኘው ተቋሙ እንዳለፉት ዓመታት ዘንድሮ ከውሉ በላይ በርከት ያሉ ጨዋታዎችን እንደማያስተላልፍ የተሰማ ሲሆን የመጀመሪያዎቹን ሁለት ሳምንታት ግን በሙሉ ለተከታዮቹ አድርሷል።
ከነገ ጀምሮ የሚደረጉት የሦስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በቴሌቪዥን ኩባንያው ሽፋን እንደማይኖራቸውና የቀጥታ ስርጭት ባለሙያዎቹ በዚህ ሰዓት ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ በሂደት ላይ እንደሆኑ አውቀናል።
[መረጃው የሶከር ኢትዮጵያ ነው]
@ARADA_SPORT @ARADA_SPORT