View in Telegram
ዶ/ር ቶማስ ላምቤ አንድ ግለሰብ ናቸው። ከ100 አመት በፊት የተከበረ የህክምና ሙያቸውንና የሞቀ ኑሯቸውን ጥለው የጅማ ህዝብ "ኢየሱስን ሳያውቅ ሊሞት ነው" በሚል ቁጭት ክርስቲያን ሊያደርጉት አዲስ አበባ ገቡ። በወቅቱ በነበረው የኦርቶዶክስ ሀገረ መንግስት ምክንያት "ወንጌል ለመስበክ" ፍቃድ ማግኘት አልቻሉምና በብላቴ ጌታ ህሩይ ምክርና እገዛ "ለመዝናናት" በሚል ሰበብ አስፈቅደው የጅማ ጉዟቸውን ጀመሩ። ጉዞው በእግር ስለነበርና መንገዱም በደንብ ግልጽ ስላልነበረ ጅማ ያሰቡት ሰው መንገድ በመሳሳታቸው ምክንያት ራሳቸውን ሀድያ ሆሳዕና አገኙት። በወቅቱ በሆሳዕና ደጃዝማች መሸሻን አገኟቸው፣ በህክምና ስራቸው ቀድመው ይተዋወቁ ነበርና ደጃዝማቹ ሀገረ ግዛቱ ላይ የጤና ተቋምና መሠል የማኅበራዊ ግልጋሎት ቦታዎችን እንዲሰሩላቸው ተማጸኗቸው። አስከትለውም የወላይታና የሲዳማ ሀገረ ገዥዎችም "ለእኛም እባክዎትን" ሲሉ ተማጸኗቸው። ጅማን በልባቸው ቢያረግዙም "እዚህም ለጊዜው ወንጌል መስራት ጥሩ ነው" በሚል ሀሳብ በሶስቱ አካባቢዎች "Instititional model" ተብሎ በሚጠራው መንገድ እየተዘዋወሩ ህክምናና ሰበካውን ተያያዙት። በኃላም እሳቸው ያቋቋሙት "አቢሲኒያ ፍሮንቲየር ሚሽን" እና በወቅቱ ስመ ጥር የነበረው "ሱዳን ኢንቲርየር ሚሽን" በጋራ በመጣመር ሶስቱን አካባቢዎች ከሞላ ጎደል ፕሮቴስታንት ማድረግ ቻሉ። ልብ ብላችኃል?ዶ/ር ቶማስ አንድ ሰው ናቸው፣ ብቻቸውን ሶስት ሰፋፊ አካባቢዎችን በጽናት "ማክፈር" ቻሉ። በዚያ የመኪና መንገድ እንኳን በሌለበት አስቸጋሪ ጊዜ በትጋት ስራቸውን ሰሩ። አንድ ሰው ቢሆኑም ማስተባበር የሚችሉበት እድል፣ ገንዘብ እና በስልጣን ካሉ ሰዎች ጋ ያለ ቅርበትን፤ ሁሉኑም በሚገባ ተጠቅመውበት ዘመን መሻገር የሚችል ስራ ሰሩ። እኛ አሁን ላይ ስንት "አንድ ሰው" አለን?ጥቂት ያልሆኑ በርካታ "አንድ ሰዎች" አሉን። ሰውን ማስተባበር፣ ገንዘብ የማዘጋጀት፣ ዳዒውን በተቋም በኩል ሰፊ ስራ እንዲሰራ ለማድረግ ወራት እንኳን የማይፈጅባቸው ጥቂት የማይባሉ "አንድ ሰዎች" አሉን። ለምን አልተሰራም?አላውቅም፣ ምናልባት እድሉ ካለፈ በኃላ በየፊናው እንወቃቀስ ይሆናል..! አላህ ግን ይጠይቀናል፣ የሰጠን እድልና አቅም ባለመጠቀማችንና በማባከናችን እያንዳንዳችንን ያለ ጥርጥር ይጠይቀናል። https://t.center/Yahyanuhe
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Find friends or serious relationships easily