View in Telegram
ከተወሰነ ወራት በፊት አንድ ስሙን የማልጠቅሰው ኢስላማዊ ተቋም ሙስሊም በዝ አካባቢ ላይ ለወጣቶች ስልጠና አዘጋጅቶ ነበር። ይህንን ስልጠና ስፖንሰር ያደረገውና በርዕሱ ዙሪያ ስልጠና እንዲሰጥ ያመቻቸው ደግሞ በሚያስደነግጥ ሁኔታ የሚሽነሪ ድርጅት ነው። ኢስላማዊ ተቋሙ ስለ ድርጅቱ በቂ መረጃ ከሌለው በሚል ወንድሜ አብዱረሒም አህመድ ጋ ተመካከክረን ለድርጅቱ አመራሮች እንዲደርስ አደረግን። ከዚያ በኃላ ተቋሙ ከሚሽነሪ ድርጅቱ ጋር ያለውን አሰራር ያቁም አያቁም ባላቅም በይፋ ያየነው ነገር አልነበረምና እንዳቆመ በማሰብ ጉዳዩን ለጊዜው ገታ አደረግነው። እንዳሰብነው በዚህ ብቻ ቢቆም ግን መልካም ነበር። ይህ የሚሽነሪ ድርጅት አሁን ደግሞ በአንድ አካባቢ ከሚሰሩ ኢስላማዊ ተቋማት ጋር በህብረት መስራቱን ገልጾ አየን። በዚህኛው ስራው ላይ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የመጅሊስ አመራሮችንም ጭምር አሳስቶ ተሳታፊ እንዳደረጋቸውም ጭምር አስተዋልን። አመራሮቹን ሆን ብለው ከፊት አምጥተው በማያቁት ነገር ቡራኬ እንዲፈጽሙላቸው አድርገዋል። የሚሽነሪ ተቋማቱ ይህኛው መንገድ ያዋጣናል ብለው የመጡ ይመስላሉ። ሙስሊሞቹ ስለነሱ እንደማናውቅ በመገመትም ይሁን ለፕሮጀክት ማስፈጸሚያ በሚሰጡን ደጎስ ያለ የገንዘብ ድጋፍ እንታተለላለን ብለው በመገመት በተለይም ሙስሊም በዝ አካባቢዎች ላይ ወጥመዳቸውን ዘርግተዋል። ኢስላማዊ ተቋማት ላይ የምትሰሩ አካላት በተቻላችሁ መጠን አብራችሁ የምትሰሯቸውን አካላት ማንነት ለማጣራት ሞክሩ። ባለማወቅ የሴራቸው መጠቀሚያ እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ። በተለይም ተቋማቱ የግብረ ሰናይ ድርጅት ሁነው ግን መሠረታቸው የውጭ ሀገር ከሆነ በደንብ ለማጣራት ሞክሩ። ድርጅቱንና አታሎ የሰራቸውን ስራዎች አስመልክቶ በቀጣይ በአላህ ﷻ ፍቃድ በዝርዝር የምንጽፍ ይሆናል። https://t.center/Yahyanuhe
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Find friends or serious relationships easily